ፔንስ እና ካሚላ ሃሪስ ክርክር አደረጉ

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ እና የዲሞክራቶቹ ተፎካካሪያቸው ካሚላ ሃሪስ በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት በተላለፈ ክርክር ላይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ የጋለ ክርክር አድርገዋል፡፡

ዕጩዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሚላ ‹‹ በሃገሪቱ ታሪኩ ከታዩ ደካማ አስተዳደሮች ቀዳሚው እንደሆነ ›› በመግለጽ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ወንጅለዋል፡፡

ማይክ ፔንስ በበኩላቸው የዴሞክራቱ ዕጩ ፕሬዝዳንታዊ ተፎካካሪ ጆ ባይደን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የያዙት ዕቅድ ከአሁኑ የኋይት ሃወስ አስተዳደር የተቀዳ ነው ብለዋል፡፡

ምርጫው የ27 ቀናት እየቀሩት በህዝብ አስተያየት መለኪያዎች ባይደን ከትራምፕ የተሸለ ዕድል እንዳላቸው እየተነገረ ነው ያለው ቢቢሲ ነው፡፡

 ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ባይደን ካደረጉት ክርክር በተሸለ የሰለጠነ መንገድ የተከተለ እንደነበር ግን ታይቷል፡፡

ፔንስ ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳደረጉት የካሚላን ንግግር በተደጋጋሚ አላቋረጡም፡፡ ፔንስ ያንን ለማድረግ በሞከሩባቸው አጋጣሚዎች ግን ወ/ሮ ካሚላ ‹‹ ይቅርታ ምክትል ፕሬዝዳንት መናገር ተራው የእኔ ነው ›› በማለት ይገስጿቸው ነበር፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 28 ቀን 2013

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *