ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከነገ ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራቸዉ ይመለሳሉ ተባለ፡፡

በያዝነው ሳምንት መግቢያ ላይ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጤና ሁኔታቸው አስተማማኝ መሆኑን ቢቢሲ የግል ሐኪማቸውን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የግል ሀኪማቸዉ ዶ/ር ሴዓን ኮንሌይ እንዳሉት አሁን ላይ ፕሬዝዳንቱ ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ የሚሰጣቸዉን ህክምና ማጠናቀቃቸዉንና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ለመጨረሻ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ከነገ ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራቸዉ መመለስና ህዝባዊ ክንዉኖች ላይ መሳተፍ ይችላሉ ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በዛሬዉ እለትም የመጨረሻ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ያደርጋሉም ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትራምፕ እንኳን ነጻ መሆናቸዉ ተነግሯቸዉ ይቅርና ገና በማገገም ላይ ሳሉ ከሆስፒታል በመዉጣት ደጋፊዎቼን ማግኘት እፈልጋለሁ በማለት በመኪና በጠዋት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ፕሬዘዳንቱ ከኮቪድ 19 ካገገሙ በኋላ ቀጣይ ተፋላሚያቸዉ ጆ-ባይደን ይሆናሉ፡፡

ህዳር ወር ላይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ እቅድ ያላት ሃያሏ ሀገር አሜሪካ የፕሬዝዳንቷ በኮቪድ 19 መጠቃት ምርጫዉ ላይ አሉታዊ ጫና እንዳያሳድር ትልቅ ስጋትን ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *