በሜድትራኒያን ባህር ወደ ጣሊያን ለመግባት የሞከሩ 11 አፍሪካዊያን ስደተኞች ሰጥመው መሞታቸው ተገለጸ።

ስደተኞቹ የተሳፈሩባት ጀልባ በቱኒዝያ የባህር ዳርቻ አካባቢ በመስጠሟነዉ ለሞት መዳረጋቸዉ ተገለጸዉ፡፡ሮይተርስ እንዳለዉ ስደተኞቹን ያሳፈረችዉ ጀልባ 30 ሰዎችን አሳፍራ እንደነበር ገልጾ 11ዱ መሞታቸዉንና የተቀሩት የገቡበት አለመታወቁን ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡ባለፈዉ ዓመትም በአካባቢዉ በተመሳሳይ አደጋ 90 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸዉን ዘገባዉ አስታዉሷል፡፡በአሁኑ ወቅት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያያዞ ሀገራት ድንበሮቻቸዉን በመዝጋታቸዉ ስደተኞቹ ወደ መጡበት ለመመለስም ሆነ ለመድረስ ወደ አቀዱበት ቦታ ለመድረስ ከፍተኛ ችግር ዉስጥ መግባታቸዉን አለማቀፋ የስደተኞች ኮሚሽን ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡በሙሉቀን አሰፋጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.