ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 178 ሚሊዮን ዶላር ከማዕድናት ገቢ መገኘቱ ተገለጸ።

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትሮ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ባለፉት ሶስት ወራት በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።ሚኒስትሩ በመግለጫቸው እንዳሉት ባለፉት ሶስት ወራት በኢትይጵያ ተመርተው ወደ ውጭ አገራት ከተላኩ ማዕድናት 178 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።ሚኒስቴሩ ባለፉት ሶስት ወራት 750 ኪሎግራም ወርቅ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ አቅዶ 2241 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ውጭ አገራት መላኩ ተገልጿል።

ለአገር ውስጥ ከቀረቡ የኢንዱስትሪ እና የኮንስራክሽን ማዕድናት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ተናግረዋል።የስራ እድልን ከመፍጠር አንጻር ደግሞ በሶስት ወራት ውስጥ ለ30 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ ተገልጿል።የኦፓል ምርትን በተመለከተ ደግሞ በባህላዊ ምርት 675 ኪሎ ግራም ተመርቶ ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን 21 ኪሎ ግራም ኦፓል ደግሞ እሴት ተጨምሮበት ለውጭ ገበያ ቀርቧል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.