የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ በጎርፍ ለወደሙ የአበባ እርሻ ኢንቨስትመንቶች ካሳ እንደሚከፍል አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ሰፋፊ ሔክታር መሬቶች በአበባ እርሻ ልማት ዘርፎች ተሸፍነዋል፡፡
ባሳለፍነው ክረምት በተለይም በአዋሽ ተፋሰስ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶች በጎርፍ ከተመቱት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።

የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራቾች ማህበር አማካሪ አቶ ዮሀንስ አበበ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በተለይም በኦሮሚያ ክልል ያሉ የአበባ እርሻ ኢንቨስትመንት በክረምቱ በጣለው ከባድ ዝናብ ክፉኛ ተጎድተናል ብለዋል።

በመሆኑም የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ለደረሱብን ጉዳት ካሳ እንዲከፍላቸው መጠየቃቸውን ተናግረዋል።

በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ በሆነው ቆቃ አካባቢ ባሉ የሆርቲካልቸር ኢንቨስትመንት ምርቶች ተመሳሳይ ችግሮች በየአመቱ ሲገጥማቸው እንደነበርም አቶ ዮሀንስ ተናግረዋል።

በአካባቢው በተደጋጋሚ የውሀውን ፍሰት የሚቆጣጠሩ እርከኖች ቢሰሩም የጎርፉን መጠን ሊቆጠጠሩ አለመቻላቸውን የተናገሩት አቶ ዮሃንስ መንግስት ተፋሰሱን እንዲያስተካክልላቸውም ጠይቀዋል።

የኦሮሚያ ክልል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዋሲሁን ጎልጋ በበኩላቸው ከማህበሩ የቀረበው ጥያቄ ትክክል መሆኑን ተናግረዋል።

ክልሉ በጎርፍ ለወደመው ኢንቨስትመንት ጥናት አድርጎ የጉዳት ካሳ ድጋፍ እንደሚያደርግ ነግረውናል።

ባለሀብቱ የሚያለማውን መሬት ዙሪያ ገባውን ከጎርፍ የሚከላከሉ እረከኖችን በማውጣቱ በዚህ አመት የተስተዋለ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ከሚያደርሰው ጉዳት በተወሰነ ደረጃ መቀነስ መቻሉንም ገልጸዋል።

በቀጣይም መሰል ኢንቨስትመንቶችን ከጎርፍ አደጋ ለመከላከል ተጨማሪ ስራዎች እንደሚከናወኑን አቶ ዋሲሁን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከኬንያ በመቀጠል አበባዎችን ለአውሮፓ እና አሜሪካ ገበያዎች ከሚያቀርቡ ጥቂት የአፍሪካ አገራት መካከል ሁለተኛዋ አገር ነች።

በተለይም ለግብርና ኢንቨስትመንት ተስማሚ የአየር ንብረት መኖሩ እና የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ማቅረቧ በርካታ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *