የኮሮና ቫይረስ በስልክ ስክሪኖች ላይ እስከ 28 ቀናት ሊቆይ ይችላል ተባለ፡፡

የአዉስትራሊያ ብሄራዊ የሳይንስ ኤጀንሲ እንዳለዉ፣ ለኮሮና ቫይረስ መንስኤ ነዉ የሚባለዉ ሳርስ ኮቭ2 ቀደም ሲል ከሚታሰበዉ በላይ የመቆየት አቅም እንዳለዉ አስታዉቋል፡፡በ20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሙቀት መጠን ላይ ቫይረሱ በስልክ ስክሪኖችና ብረት ነክ በሆኑ ቁሳቁሶች ላይ እስከ 28 ቀናት እንደሚቆይ ተቋሙ ገልጧል፡፡ቀደም ሲል ቫይረሱ በነዚህ ቁሳቁሶች ላይ ከ3 እስከ 4 ቀናት ብቻ ሊቆይ እንደሚችል ነበር የሚታመነዉ፡፡ሙቀቱ ከፍተኛ በሆነባቸዉ አካባቢዎች ላይ ግን የቆይታ ጊዜዉ በእጅጉ ያጠረ መሆኑን የገለጸዉ ተቋሙ፣እስከ 40 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሙቀት ባለበት አካባቢ ደግሞ አንድ ቀን ብቻ ሊቆይ ይችላል ተብሏል፡፡ከዚህ ቀደም ተከስቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነዉ ፍሉ ቫይረስ በተመሳሳይ ቁሳቁሶች ላይ እስከ 17 ቀናት ብቻ የመቆት አቅም እንደነበረዉ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8በሙሉቀን አሰፋጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *