የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ 3 ሺህ 500 የጎዳና ተዳዳሪዎችን እንደሚያነሳ አስታወቀ።

የከተማዋ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ሐላፊ አቶ ተፈራ ሞላ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት እስካሁን ከ9 ክፍለ ከተሞች 1 ሺህ 148 የጎዳና ተዳዳዎች ተነስተው ቃሊቲ ማቆያ እና ማገገሚያ ማእከል እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

የተሱትን የጎዳና ተዳዳሪዎች ተገቢውን የስነልቦና ትምህርት ስልጠና በመስጠት በከተማው ዉስጥ ባሉ የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ዉስጥ በማስገባት እንደየፍላጎታቸው ሰልጥነው ወደ እንደሚገቡም ተገልጿል።

ባለፉት አመታት ከጎዳና ላይ ከሰበሰባቸው በኋላ በተለያየ ችግሮቺ ምክንያት መልሰው የመውጣት ችግሮች ያጋጠመው መሆኑን የነገሩን አቶ ተፈራ ይሄን ችግር ለመቅረፍ በቅድሚያ ግንዘቤ የማስጨበጥ ስራ እየተሰራ መሆኑን እና በሚፈልጉበት የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩ እየተደረገ መሆኑን ገልፀውልናል፡፡

ሃላፊው አክለውም ባብዛኛው ከጎዳና ላይ እየተነሱ ያሉ ሰዎች ዲግሪ እና ከዛ በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው እንደሚገኙበትም ነግረዉናል፡፡

በመጨረሻም ይህ ፕሮጅክት ለማከናወን የሚውል ከአለም ባንክ 270 ሚሊየን ብር ድጋፍ መገኘቱንም ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሁሉሀገር አተሮ
ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *