የአፍሪካ ትልቁ ተራራ ኪሊ ማንጃሮ ተራራ ቃጠሎ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

በተራራው ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት 500 ያህል የእሳት አደጋ ሰራተኞች መሰማራታቸው ተገልጿል፡፡

ከሁለት ቀናት በፊት ታንዛኒያ ውስጥ በሚገኝው የአፍሪካ ረጅሙ ተራራ ኪሊ ማንጃሮ ተራራ የተነሳው የእሳት አደጋ ከፍተኛ ቦታ እየሸፈነ መምጣቱን ነው የተነገረው፡፡

በዚህም የሀገሪቱ መንግስት ከተለያዩ መስራቤት የተውጣጡ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ወደ ተራራው እንዳሰማራ ነው የተገለጸው፡፡

የታንዛኒያ ብሔራዊ ፓርክ እንዳስታወቀው የእሳት አደጋ ሰራተኞቹ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ አስታውቆ እሳቱን በቁጥጥር ስር እያዋሉት ይገኛሉ ብሏል፡፡

የፓርኩ ዳይሬክተር ፓስካል ሺሉቴት ለአልጀዚራ እንደተናገሩት የአደጋው መንስኤ ምን እንደ ሆነ እስካሁን አልታወቀም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኪሊ ማንጃሮ በአፍሪካ ትልቁ ተራራ ሲሆን ከመሬት ጠለል በላይ 19 ሺህ 443 ሜትር ርቀት አለው፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *