የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው ህሙማኑን ለሞት ያበቃቸው መድሀኒታቸውን በማቋረጣቸው ነው።
የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ፅጌርዳ ክፍሌ እንዳሉት መገናኛ ብዙሀን አብዛኛውን ጊዜያቸውን ለኮቪድ -19 መስጠታቸው ኤች አይ ቪ ኤድስ እንዲዘነጋ ምከንያት ሆኗል።
እናም ሁሉም መገናኛ ብዙሀን ሁለቱንም በተመጣጣነ መልኩ ሽፋን እንዲሰጡ አሳስበዋል።
የኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማን መድሀኒታቸውን በአግባቡ እንዲወስዱ ያሳሰቡት ዶክተር ጽጌረዳ የህክምና ተቋማትም ችግሩን በደንብ እንዲያጤኑትም ጠይቀዋል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም











