በደቡባዊ ህንድ በጣለ ከባድ ዝናብ የ16 ስዎች ህይወት አለፈ።

በሃገሪቱ ደብባዊ ክፍል በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ቢያንስ 16 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ባለስልጣናት እና የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሃገሪቱ በሃይድራባድ በተሰኘ ግዛትና አካባቢው ላይ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውንና እንደ ሃገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ በጎርፍ የሁለት ወር ህፃን ልጅ ህይወት ማለፍን ጨምረዋል ገልፀዋል ፡፡

በህንድ በተደጋጋሚ እየጣለ ባለው ከፍተኛ ዝናብ ሳቢያ ከፍተኛ ውድመትና ሞት ደርሷል ፡፡

ዝናቡ በጥጥ ፤በጥራጥሬ ና በሌሎችም ሰብሎች ላይ ጉዳት ማድረሰም ተነግሯል፡፡

በሃገሪቱ ካለፈው ሰኔ ወር አንስቶ እስከ መስከረም አጋማሽ ባለው ጊዜ ውስጥ ከዝናብ ጋር በተያያዙ ክስተቶች ከ 1 300 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የህንድ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በደቡብ እስያ በመላው አገሪቱ ከ 9.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዚህ ዓመት በከባድ ጎርፍ ተጎድተዋል ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ምግብና መድኃኒት ለማግኘት መቸገራቸውንም
አልጀዚራ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በየውልሰው ገዝሙ
ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.