የውጭ ዜና

የቡድን 20 አባል ሀገራት ለደሃ ሀገራት የእዳ መክፈያ ጊዜን ለ6 ወራት አራዘሙ፡፡

የአለም ግዙፍን ኢኮኖሚ ድርሻ የሚይዙት እነዚህ የቡድን 20 አባል ሀገራት፤ ኮሮና ቫይረስ አለም ላይ ባደረሰው የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል እና በበሽታው እጅግ ተጋላጭ የሆኑ ደሃ ሀገራትን ለመርዳት በሚል የእዳ መክፈያ ጊዜዉ እንዲራዘም መወሰናቸዉን ዥንዋ ዘግቧል፡፡

ሀገራቱ እዳቸወን ለመክፈል ከመጨነቅ ይልቅ በሽታውን መከላከል ላይ እንዲያተኩሩ በሚል ለተጨማሪ 6 ወራት ተራዝሞላቸው እንዲከፍሉ ተስማምተዋል፡፡

የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ሃለፊዋ ክሪስታሊና ጂዎርጄቫ እንደተናገሩት፤ ‹‹ኮቪድ 19 ይዞት በመጣ ችግር የአለም ኢኮኖሚ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ፤ በሳምንታት ጊዜ ብቻ በ85 በመቶ እንቅስቃሴው ቆሞ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ይህ ደግሞ ለደሃ ሀገራት ተጽዕኖው ከባድ በመሆኑ፤ ሀገራቱ በሽታውን የመከላከል አቅማቸውን ለመጨመር፤ ከቡድን 20 አባል ሀገራት ጋር ተነጋግርን እስከ መጨረሻው የሰኔ ወር እ.ኤ.አ 2021 ድረስ ብድር የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ወስነናል ብለዋል፡፡

በዚህም ሀገራት የጤና ስርዓታቸዉን ማጠናከርና አስቸኳይ ለሆኑ ችግሮቻቸዉ መልስ መስጠት ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በጅብሪል ሙሃመድ
ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *