የኦሮሚያ ፖሊስ አቶ ልደቱ አያሌውን በቀጥታ እንዲፈታ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አሰተላላፈ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የሶስት ምስክሮችን ቃል የሰማ ሲሆን በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ የቀጠረውን ትዕዛዝ የቢሾፍቱ ፖሊሲ መምሪያ ለምን እንዳላከበረ ፍርድ ቤት መጥቶ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ቢሰጠውም አንድም አስረጂ አልቀረበም ብለዋል ለኤትዮ ኤፍ ኤም የኢዲፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ።

በሌላ በኩል በተደጋጋሚ ትዕዛዝ አላከብር ያለው የቢሾፍቱ ፖሊሲ መምሪያ ትዕዛዙን ለምን ማክበር እንዳልቻለ አቶ ልደቱ አያሌውን አጅቦ በመጣው ሳጅን መሀመድ አሊ በኩል ትዕዛዙ እንዲረሰው ትዕዛዝ አስተላልፋል።

ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *