በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያሉበት ሁኔታን እንደሚፈታ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላለፍት 20 ቀናት ሲስሩ የሰነበቱ ጉዳዬች ላይ ማብራሪያን ሰተዋል።

ኢትዮጲያ በ75 ተኛው የተባበሩት መንግስት ድርጅት የነበራትን ተሳትፎ ፣የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የልኡካን ብድን በሱዳን ስለአደረገው መጠነኛ እርዳታና ገብኝት እንዲሁም በቅርብ ስለተከናወኑ የአምባሳደር ሹመቶች ላይ ገለፃ ተደርጓል።

በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ውስጥ ከ 900 በላይ ዜጎች ከውጪ ሃገራት ስለ መመለሳቸው ተነግሯል።

በጋዜጠኞችም በተደጋጋሚ በሳውዲ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያሉበት ሁኔታ ምን ይመስላል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ታሳሪዎቹ ካሉበት ሁኔታ ነፃ ለማውጣትስ ምን እየሰራ ነው ?የሚለው ጉዳይ በተደጋጋሚ ተነስቷል።

በሳውዲ ብቻም ሳይሆን በተለያዩ መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ አሳዛኝና መፍትሄ ሊበጅለት የሚገባ ነው ያሉት አምባሳደር ዲና ከሃገራቱ ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን በማድረግ ችግሩን ለመፍታት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ሌላው በመግለጫው ላይ የተነሳው የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ጉዳይ ሲሆን የፕረዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ጉብኝት አላማና ሃገራቱ ያልተቋጩ የዲፕሎማሲ ጉዳዬች በተለይም በድንበር ጉዳይ ላይ ምን ታስቧል? ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ሃገራቱ በጊዜ ሂደት ያላቸው ግንኙነት እየ ዳበረ መምጣቱና በቀጣይም የተሻለ ቅርርቦሽ እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

በየውልሰው ገዝሙ
ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.