በአዲስ አበባ የፓርኪንግ ቦታዎችን ለሌላ አገልግሎት ባዋሉ 30 ህንፃዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በከተማዋ በሚገኙ 30 ህንጻዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

ኤጀንሲው እርምጃውን የወሰደው ከከተማዋ ግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን ጋር በመሆን ሲሆን 200 ህንፃዎች ላይ ለፓርኪንግ የተዘጋጁ የህንፃ ስር ፓርኪንግ ቦታ አጠቃቀም ላይ ፍተሻ አድርጎ ነው።

በዚህም 30ዎቹ ከታለመለት ዓላማ ውጭ እየተጠቀሙበት እንደሆነ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

የፓርንግ ቦታዎቹን ለሌላ ዓላማ ያዋሉ የህንፃ ባለቤቶች የቃል እና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡

የፓርኪንግ ቦታዎቹን ለታለመላቸው ዓላማ ተግባራዊ የማያደርጉ የህንፃ ባለቤቶች ላይ በንግድ ቢሮ በኩል ንግድ ፈቃዳቸው እንዲነጠቅ እና ህንፃዎቹ አገልግሎት እንዳይሰጡ እስከማሸግ የሚያደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው፡፡

ኤጀንሲው የህንፃ ስር ፓርኪንግ አጠቃቀምን ወደ ስርዓት በማስገባት ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ እና የመንገድ ላይ ፓርኪንግ አገልግሎት አሰጣጥ በማህበራት ተደራጅተው አገልግሎት የሚሰጡት በኤጀንሲው ደረሰኝ እንዲጠቀሙ የማድረጉ ሂደት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ሲልም አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.