ትናንት ምሽት በብሔራዊ ባንክ የተከሰተው ምንድን ነው

ትናንት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በብሔራዊ ባንክ የእሳት አደጋ መከሰቱ ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንን ጠይቋል።

በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጉልላት ጌታነህ እንዳሉን አደጋው የደረሰው በብሔራዊ ባንክ መጋዘን ወይም ስቶር ውስጥ ሲሆን በተፈጠረው አደጋ 50 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም አንድ ሚሊዮን የሚገመት ንብረትን ደግሞ ከውድመት ማዳን ተችሏል።

የአደጋው መንስኤን በመጣራት ላይ መሆኑንም አቶ ጉልላት ነግረውናል።

አደጋውን ለመቆጣጠር የኮሚሽኑ አደጋ መቆጣጠር ሰራተኞች ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር እሳት አደጋው የባሰ ጉዳት ሳያደርስ በ27 ደቂቃ ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንም ተናግረዋል ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.