የአውሮፓ አገራት ኢኮኖሚ በያዝነው ዓመት በ8.3 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ አስታወቋል፡፡

ድርጅቱ ባወጣው መረጃ መሰረት የዩሮዞን ኢኮኖሚ በ2020 አመት ከፍተኛ ቅናሽ ያደርጋል፡፡

የአዉሮፓዊያኑ ኢኮኖሚ ማንሰራራት ከመጀመሩ በፊት ሰኔ ወር ላይ ያጋጥማል ተብሎ ከተገመተው 10.2 በመቶ ተሻሽሎ ወደ 8.3 በመቶ ዝቅ ማለቱንም አንስቷል፡፡

ድርጅቱ ውድቀቱን ከ1930ዎቹ ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ብሎ በመግለፅ ለወረርሽኙ የህክምና መፍትሄ ካልተገኘ በ2021 ሰኔ ላይ ከተገመተው የ6 በመቶ ኢኮኖሚያዊ እድገት በ5.2 በመቶ ብቻ ሊጨምር እንደሚችል ገልጧል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ በ2021 የ6.1 በመቶ ጭማሬ እናያለን በማለት ሙሉ ሀሳቡን አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም ከተነበየው ጠንከር አድርጎ አስቀምጧል፡፡

በዚህ ዓመትም ስፔን 12.8 በመቶ ጠቅላላ የሃገራዊ ምርት ቅናሽ ስታሳይ፣ ጣሊያን 10.6 በመቶ አንዲሁን ፈረንሳይ 8.3 በመቶ የጠቅላላ ሀገራዊ ምርታቸዉ ያሽቆለቁላል ተብሏል፡፡

እንግሊዝ በዓንጻሩ የ9.8 በመቶ ቅናሽ ስታደርግ በቀጣይ የፈረንጆች ዓመትም የ5.9 በመቶ እድገት በማድረግ ታገግማለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሁሉአገር አተሮ
ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *