የፌዴራል የህግ ታራሚዎች የቤተሰብ ጉብኝት ከነገ ጀምሮ እንደሚጀምር ተገለፀ፡፡

የፌዴራል የህግ ታራሚዎች ከነገ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለወረርሽ በማያጋልጥ መንገድ በቅርብ ቤተሰቦቻቸው እንደሚጎበኙ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

አዲስ በወጣው መመሪያ መሠረት ቅዳሜና እሁድ አንድ ታራሚ በአንድ ቀን በአንድ የቅርብ ቤተሰብ ብቻ ይጎበኛል፡፡

መጠየቅ የሚችሉት የታራሚ ቅርብ ቤተሰብ ማለትም ባል፣ ሚስት፣ ልጅ፣ እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም፣ አንድ የቅርብ ጓደኛ እና የኃይማኖት አባት መሪ ብቻ ናቸው ነው ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ጠበቆችና የወጪ ሃገር ዜጎች እስረኞችን ለመጎብኘት ከኢንባሲዎችና ከቆንፅላዎች ለሚመጡ ገደብ ሳይደረግ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግና እርቀታቸውን ጠብቀው እንዲስተናገዱ ይደረጋልም ሲል ነውመሠረት ያስታወቀው፡፡

ምግብ የሚገባውም በጎብኝዎች ብቻ ይሆናል ተብሏል፡፡

በሆስፒታል ለሚገኙ ህሙማን ታራሚዎችን በህክምና ባለሙያዎች በሚሰጥ መመርያ የሚንከባከብ አንድ አስታማሚ እና ምግብ እንዲገባ ይፈቀዳል፡፡

የእስረኛ ጠያቂዎች የአፍና የአፍንጫ ጭንብል ማድረግና ተቋሙ ባዘጋጃቸው የእጅ ንጽህና መጠቀሚያ ቦታዎች መታጠብ ይገባቸዋልም ተብሏል፡፡

ከሁለት መቶ ብር በላይ ለእስረኞች መስጠትም የማይቻል ሲሆን ከሁለት መቶ ብር በላይ መስጠት የሚፈልጉ ጉብኝዎች በታራሚዎች አካውንት ውስጥ ማስገባት እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡

በዝዋይ እና በሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች ቅዳሜና እሁድ እንዲጎበኙ እንደሚፈቀድላቸው እና በአንድ ጊዜ ከሁለት ያልበለጡ ጎብኚዎችም እንዲጎበኙት ይፈቀድላቸዋል ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.