11 ሚሊዮን ሴቶች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ ላይመለሱ ይችላሉ ሲል ዩኔስኮ ስጋቱን ገለጸ፡፡

የዩኔስኮ ዳይሬክተር ጀነራል ኦድሬይ አዙላይ በኮንጎ ግብኝት ሲያደርጉ እንዳሉት ሀገራት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመለሱ እየገፋፉ ቢሆንም ከ11 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሴቶች አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸዉ ላይመለሱ ይችላሉ ብለዋል፡፡

ይህም የሚሆነዉ የኮሮና ቫይረስ በፈጠረዉ ተጽዕኖ ምክንያት ሴቶች በቤት ዉስጥ ስራ መጠመዳቸዉን ጠቅሰዋል ሃላፊዋ፡፡

መንግስታትም ቢሆን በመማሪያ ክፍሎችና የቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተገቢዉን ክትትል ላያደርጉ እንደሚችሉ ጠቅሰዉ እነዚህ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸዉ ለመመለስ ከፍተኛ የግንዛቤ ማስጨበጫና የቅስቀሳ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን ፕረስ ትቪ ዘግቧል፡፡

የዓለም ባንክና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማትን የሃገራትን ችግር በመመልከት በተለይም ችግሩ ለበረታባቸዉ ከሰሃራ በታች ለሚገኙ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባም ሃላፊዋ አሳስበዋል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *