የዩንቨርሲቲው ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከቀናት በኋላ 4 ሺህ ተመራቂ ተማሪዎችን ይቀበላል።
ኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ተማሪዎቹ አንድ ሴሚስተር ሲቀራቸው በመሆኑ መመረቅ የሚያስችላቸውን የአራት ወራት ትምህርት በሁለት ወር ውስጥ መስጠት የሚያስችል ስርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶ መጠናቀቁንም ዶክተር ቀነኒሳ ነግረውናል።
ተማሪዎቹ በኮሮና ቫይረስ እንዳይጠቁ የመማሪያ ክፍሎችን፣ ቤተ መጽሀፍት፣መመገቢያ እና መዝናኛ ስፍራዎች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መንገድ ማከናወን የሚያስችል የቁሳቁስ እና የሰው ሀይል በሚገባ ዝግጅት መደረጉን ምክትል ፕሬዘዳንቱ ገልጸዋል።
ይህ ሁሉ ዝግጅት ተደርጎም በቫይረሱ የሚጠቁ ተማሪዎች ቁጥር ከጨመረ ህክምና ማካሄድ የሚያስችል ዝግጅቱም ከበቂ በላይ ተዘጋጅተናልም ብለዋል።
ባንድ ክፍል ውስጥ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎችን ከ20-25 ከማድረግ በተጨማሪ ትምህርታቸውን በኦንላየን መከታተል የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውንም ዶክተር ቀነኒሳ ተናግረዋል።
ዩንቨርሲቲው ኮሮና ቫይረስ ከመግባቱ በፊት 47 ሺህ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች በማስተማር ላይ የነበረ ሲሆን 4 ሺህ ያህሉ ተመራቂ ተማሪዎች ናቸው።
እነዚህ ተመራቂ ተማሪዎች የሚመረቁበት ቀን የዩንቨርሲቲው ሴኔት በቀጣይ በሚያስቀምጠው ውሳኔ መሰረት ይታወቃል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23-30 የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንደሚያደርጉ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በሳሙኤል አባተ
ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም











