በቱሪስት ቪዛ ሰበብ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት እየወጡ እንደሆነ ተገለጸ።

በኮሮና ወረርርሽኝ ምክንያት ሁሉም ሀገራት ከሌሎች ሀገራት የሚመጡ ሰራተኞችን መቀበል ማቆማቸው ይታወቃል፡፡

ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይም በዚህ ምክንያት የስራ ስምሪት ወደ ተለያዩ ሀገራት እየላከ እንዳልሆነ የሚታወቅ ቢሆንም ጣቢያችን ከተላያዩ ሰዎች በተደጋጋሚ በደረሰው ጥቆማ አማካኝነት ኤጀንሲዎች በቱሪስት ቪዛ ለጉብኝት እንደሚሄዱ አድርገው ወደ አረብ ሀገር ዜጎችን ለስራ እየላኩ እንደሆነ ሰምተናል፡፡

እኛም ወደ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ አቅንተን ምን ያህል ቁጥጥር እያደረጋችሁ ነው ስንል ጠይቀናል፡፡

በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጪ ሀገራት ስራ ስምሪት ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሀኑ አበራ እኛም ጥቆማው ደርሶናል ፤ እርምጃም እየወሰድን ነው ብለዋል፡፡

የተባበሩት አረብ ኤምሬት በራራ ቢጀምርም ገና ሰራተኛ መቀበል አልጀመረም የሚሉት አቶ ብርሀኑ የስራ ቅጥር ቪዛ ነው ብለው ለማጭበርበር የሞከሩ አሉ ብለውናል፡፡

ለማጭበርበር ከሞከሩት ኤጀንሲዎች ኤክሰርሳይስ የተባለው አንዱ ነው፤ ፍቃድ ከመንጠቅ አንስቶ በህግ እስከመጠየቅ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ ተናግረዋል ጀነራል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

በዚህ በኩል ቁጥጥራቸውን እንዲያጠብቁም ለኢሚግሬሽን ደብዳቤ ፅፈናል ሲሉም ነግረውናል፡፡

የስራ ስምሪቱ ሲጀመርም ከኢምግሬሽን ጋር በትብብር ከመስራት በዘለለ የራሳችንን ሰው በማቆም በጥብቅ ለመቆጣጠር አቅደናል የሚሉት አቶ ብርሀኑ ለስራ ወደ ውጪ ሀገራት መሄድ የምትፈልጉ ዜጎቻችን እባካችሁን ለኤጀንሲዎች ገንዘባችሁን ማበከናችሁን ትታችሁ በህጋዊ መንገድ ክብራችሁን ደህንነታችሁ ተጠብቆ ተጓዙ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በህገ ወጥ መንገድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በምናይበት ጊዜ በመጠቆምም ሆነ በሌላ መንድ ተባብረን እናስቁም ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ይህንና ዳይሬክተሩ ይሄንን ይበሉ እንጂ ይሄንን ዘገባ እስከሰራንበት ጊዜ ድረስ በርካታ ዜጎቻችን በቱሪስት ቪዛ በሚል በህወጥ ደላሎች ተታለው አሁንም ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት በማምራት እራሳቸውን ለዘራፊዎች በማጋላጥ ላይ ናቸው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.