በአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ በሚል ስራ ይጀምራሉ የተባሉት ከ560 አውቶቢሶች ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት 560 የግል ማህበራት አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚያስገባ ማሳወቁ ይታወሳል።

በከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትይ ኤፍ ኤም እንዳሉት እነዚህ አውቶቢሶች እስካሁን ድረስ ወደ አገልግሎቱ አልገቡም።

አውቶቡሶቹ አገልግሎቱን ለመጀመር የስምሪት ቦታቸውን በተመለከተ መረጃ እየተሰጣቸው መሆኑን ነግረውናል፡፡

ሆኖም ከሰዓት በኋላ ስምሪታቸውን ሲያወቁ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጡ ይስተዋላሉ ተብሏል፡፡

አውቶቢሶቹ ወደ ትራንስፖርት አገልግሎቱ የገቡት በከተማ አስተዳደሩና በግሉ ዘርፍ ትብብር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ከአሁን ቀደም በየወሩ ለብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት 58 ሚሊየን ብር ድጎማ በማድረግ ላይ ሲሆን አሁን ደግሞ ለአውቶቡሶች ኪራይ 63 ሚሊየን ብር በጠቅላላው 121 ሚሊዮን ብር ድጎማ እንደሚያደርግ ቢሮው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጿል፡፡

በቀጣይ ሁለት ዓመታትም በ12 ቢሊዮን ብር ወጪ 3 ሺህ የሚሆኑ አውቶብሶችን በግዢ ለማስገባት የከተማ አስተዳደሩ በሂደት ላይ መሆኑንም ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በደረሰ አማረ
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.