በአዲስ አበባ ገላን ወንዝ ላይ አንድ የ43 አመት ጎልማሳ ወንዝ ውስጥ ሕይወቱ አልፎ ማግኘቱን የአዲስ አበባ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ገላን ወንዝ ላይ የ43 አመት ጎልማሳ ሕይወቱ ማለፉ በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት 2 ሰ ሰዓት ከ 42 ደቂቃ ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ገላን ወንዝ ላይ የ 43 አመት ጎልማታሳ ሕይወቱ ማለፉ ተገልጿል፡፡

የሞቱ መንስኤን ምን እንደሆነ ለጊዜው አለመታወቁን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 አስኮ ገብርኤል አካባቢ አንድ ሱቅ ላይ በደረሰ እሳት አደጋ የ20 ሺህ ብር ንብረት የወደመ ሲሆን የኮሚሽኑ ሰራተኞች ባደረጉት ጥረት ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከውድመት መታደግ መቻሉን ተገልጻዋል፡፡

በአንድ ሰው ላይ መጠነኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ፣ የአደጋው መንስኤ እስካሁን ድረስ እንዳልታወቀ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በዳንኤል መላኩ
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *