በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች በኤች አይቪ ኤድስ እንደሚሞቱ ተገለጸ።

የፌዴራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት እንዳሳወቀው የኮሮና ቫይረስ መግባትን ተከትሎ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና በእጅጉ ተቀዛቅዟል።

ህክምናውን ማግኘት ከሚገባቸው 531 ሺህ 149 ሰዎች መካከል ክትትል እያደረጉ ያሉት 459 ሺህ 67 ብቻ ናቸው።

ከነዚህ መካካል 17 ሺህ ነፍሰጡር ሴቶች ሲሆኑ 18 ሺህ ያህሉ ደግሞ ህጻናት ናቸው።

የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና ለማድረስም በዘንድሮው የእቅድ ዘመን 8 ሚሊየን 276 ሺ 33 ሰዎች በመመርመር 90 ሺህ ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ለመለየት ዕቅድ ተይዟል።

በኢትዮጵያ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ዜጎች 669 ሺህ 219 ሲሆን አዲስ አበባ፣ጋምቤላ፣አፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በአንጻራዊነት ቫይረሱ የተስፋፋቸው ክልሎች ናቸው።

ጽህፈት ቤቱ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ካለፉ ዜጎች ውስጥ 28 በመቶዎቹ የኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማን እንደሆኑ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *