ኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል የሚረዱ የፀረ አንበጣ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ከቻይና ተረከበች።

ኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል የሚረዱ ተሸከርካሪዎችንና ሌሎች የፀረ-አንበጣ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ከቻይና መረከቧን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በድጋፍ መልክ የገኘችው የፀረ-አንበጣ መንጋ ቁሳቁሶች፣ የፀረ ታህዋሲያንን እና ፀረ ተህዋስያንን ለመርጨት የሚረዱ መኪኖችና በርጭት ወቅት ጥቅም ላይ የሚውሉ ጭምብሎችን ነው፡፡

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ወቅት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ እንዳሉት፣ ቻይና ድጋፉን ያደረገችው በሀገር አቀፍ ደረጃ የአንበጣ መንጋን የመከላከል ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ነው፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ወዳጅነት የመሰረቱና በግብርና ዘርፍ በትብብር እየሰሩ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው ቻይና ለኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍና የምግብ እርዳታ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኗን ጠቁመዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ቻይና ኢትዮጵያ እንድትበለፅግና ረሷን እንድትችል በምትችለው መጠን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑንም መናገራቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.