ህብረቱ በኩባንያዉ ላይ ምርመራ ይደረጋል ያለዉ በዋናነት የልጆች የግል ፋይል ደህንነትና ለድህንነታቸዉ ሲባል በሚተገብራቸዉ ክልከላዎች ላይ ነዉ ተብሏል፡፡
ከዚህ ባሻገርም ኢንስታግራም የግለሰብና ኩባንያ የግል መረጃዎችን አይደብቅም፣ሁሉም እንዲመለከታቸዉ እያደረገ ነዉ የሚሉ ክሶችም እንደቀረቡበት ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በዚህም ህብረቱ ምርመራ አደርጋለሁ ያለ ሲሆን ምርመራዉን የአየር ላንድ የመረጃ ጥበቃ ኮሚሽን ያከናዉነዋል ተብሏል፡፡
የቴክኖሎጂ ኩባንያዉ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል ነዉ የተባለዉ፡፡
ኢንስታግራም ህጻናት ማየት የማይፈቀድላቸዉን ፋይሎች ሁሉ ለህጻናት እንዲያዩት ይፈቅዳል በሚል የሚተች ሲሆን በምርመራዉ ህጻናት እንዲያየዋቸዉ የማይፈቀዱ ፋይሎችን በሚመለከት ያስቀመጠዉ የክልከላ መተግበሪያም አብሮ ይታያል ተብሏል፡፡
ኢንስታግራም አካዉንት ለመክፈት የሚጠየቀዉ ትንሹ እድሜ 13 ዓመት ነዉ፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በሙሉቀን አሰፋ
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም











