የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች በፌደራል የአስተዳደር ስነ_ስርአት አዋጅ ዙሪያ በመወያየት ላይ ናቸው።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው በዚህ ውይይት ላይ ከአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በህግ ሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ጨምሮ አመራሮች ተገኝተዋል።

ምክክሩ ከዛሬ ጥቅምት ጀምሮ ለቀጣዮቹ አምሰት ቀናት ይቀጥላል ተብሏል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህር ቤት መምህር የሆኑት ዶክተር መሃሪ ረዳኢ እና ዶክተር ሰለሞን ዓባይ የምክክር መድረኩን በመምራት ላይ ይገኛሉ።

መድረኩ በዛሬው እና ነገ ውሎው በአዋጁ አስፈላጊነት፣ ያስተዳድር መመሪያዎች አወጣጥና አፈጻጸም እንዲሁም የፍርድ ቤት ክላሳ ስነ_ስርዓት እና በልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በጅብሪል ሙሃመድ
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.