ፍርድ ቤቶች የሚሰጡትን ማንኛውም ውሳኔዎች አስፈጻሚው አካል ማክበር እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳሰቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት እኛ ያላከበርነው እና ያልታዘዝነው ፍርድ ቤት ነጻና ገለልተኛ ሆነ ማለት ከንቱ ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ዛሬ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የለውጥ ሀይሉ የፍትህ ስርአቱ ከፖለቲካ ጫና ነጻ እንዲወጣ ራሱን ችሎ እንዲፈርድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የምርጫ ቦርድ በአንድ እግራቸው እንዲቆሙ የሰራው ስራ ተስፋ ሰጪ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

ነገር ግን የፍትህ ስርአቱ ገለልተኛ ፤ነጻ ይሁን ያለው ይህ ሀይል የፍትህ ውሳኔዎችን የሚቃረን መሆን የለበትም በአስቸኳይ መታረም አለበት ነው ያሉት፡፡

አሁንም ቢሆን ያልተፈቱ ድክመቶች እንዳሉ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፍርድ ቤቶች ለሚሰጧው ውሳኔዎችና ብያኔዎች ምንም ሳያወላዳ መቀበል ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡

አሰፈጻሚው አካል ላይ ያለው ወንጀለኛን መደበቅ እና አልታዘዝም ማለት ፈጥኖ መታረም ያለበት ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

አስፈጻሚው አካል በጥንቃቄ ማየት ያለበት ሌላኛው ጉዳይ በተለይ ባለስልጣናት የግል ክብርና ማንነት ከቢሮ ሲወጡ መተው አለባቸው ፡፡

ሰዎች መናገር ፣መጻፍ እና መተቸት እንዲችሎ መፍቀድ ይኖርብናልም ብለዋል፡፡

መፍቀድ የሌለብን የሀገሪቱን ሉአላዊነት ፤አንዱን ከአንዱ የሚያጋጭ ፣ የሚያነሳሳ ከሆነ እንጂ በብዕራቸው ሰዎች እኛን መተቸት ስለእኛ መጻፍ ይችላሉ አስፈጻሚው ይህንን በሆደ ሰፊነት መመልከት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

በያይኔ አበባ ሻምበል
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *