በአርጀንቲና በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊየን ተሻገረ።

ሀገሪቱ አንድ ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ያረጋገጠች አምስተኛዋ የአለም ሀገር ሆናለች፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ አጠቃላይ ቁጥሩን ወደ 1 ሚሊየን ሁለት ሺ 662 ያደረሰው 12 ሺኅ 982 አዳዲስ የተጠቂዎች ቁጥር እንደሆነ የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል ፡፡

እንዲሁም በ24 ሰአት ውስጥ የ451 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ የሟቾችን ቁጥር 26 ሺህ 716 ደርሷል፡፡

45 ሚሊዮን የሚጠጋ የህዝብ ብዛት ያላት አርጀንቲና ትንሽ ህዝብ ይዛ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተጠቂዎችን በማስመዝገብ የመጀመሪያዋ የአለማችን አገር ሆናለች፡፡

አርጀንቲና አሜሪካንን፣ ህንድን ፣ ብራዚልን እና ሩሲያን በመከተል በርካታ ህዝብ የተጠቃባት አገር ተብላለች።

በዓለማችን ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በኮሮና ቫረስ የተጠቁ ሲሆን ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ መሞታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *