በኢትዮጵያ 250 ሺህ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ኪት መመረቱን ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ።


ኢትዮጵያ ቢጂአይ ባዮ ቴክኖሎጂ ከተባለው ግዙፍ የቻይና ኩባንያ በመተባበር ያቋቋመችው የኮሮና መመርመሪያ ፋብሪካ መስከረም 3 ቀን 2013 ዓ.ም በጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር አቢይ አሕመድ ተመርቆ መከፈቱ ይታወሳል።

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፖርክ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በአመት 10 ሚሊዮን የመመርመሪያ ኪቶችን የማምረት አቅም እንዳለውም በምረቃው ወቅት ተገልጾ ነበር።

ዶክተር ሊያ ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ይህ ፋብሪካ እስካሁን 250 ሺህ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ኪት ማምረቱን ተናግረዋል።

ፋብሪካው በአመት ከ10 ሚሊዮን በላይ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን ኪቱ ለኢትዮጵያ እና ለተቀረው የአፍሪካ አገርም ትልቅ አቅም መሆኑም ተገልጿል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *