በምስራቃዊ ዛምቢያ ክልል በሚገኝ ኒምባ በተባለ መንደር 12 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መያዛቸውን የአካባቢው ኢሚግሬሽን መምሪያ አስታውቋል፡፡
የዛምቢያ መንግስት እንዳስታወቀው ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ጉዞ ላይ የነበሩ ሲሆን 6 የዛምቢያ ዜግነት ያላቸውን ጨምሮ ሌሎች 15 ስደተኞችም አብረዋቸው እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
ከተያዙት 12 ስደተኞች በተጨማሪ በትናንትናው እለትም 27 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሚኒባስ መኪና ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ሲሞክሩ በክልሉ ፖሊስ መያዛቸው ተገልጿል፡፡
እንደ አውሮፓውያኑ በተያዘው አመት ከመስከረም ወር ወዲህ በዛምቢያ የህግ-ወጥ ሰዎች ዝውውር መበራከቱን ሉሳካ ታይምስ በድረገፁ አስነብቧል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በሁሉአገር አተሮ
ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም











