ቻይና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻንጋይ እንዳይበር እገዳ ልትጥል እንደምትችል አስጠነቀቀች።

የቻይና ሲቪል አቪዬሽን ተቆጣጣሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሻንጋይ በረራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እጅግ የከፋ የበረራ እገዳ ውሳኔ ልታስተላልፍ እንደምትችል አስጠንቅቃለች።

የቻይናው ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር በትናንትናው እለት የበረራ ቁጥሩ ኢቲ 688 ከጥቅምት 26 ጀምሮ በረራ እንዳያደርግ ይታገዳል ብሏል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ በዚህ በረራ ቁጥር መተው የነበሩ ተሳፋሪዎች በኮቪድ 19 መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ነው፡፡

ነሀሴ 31 ላይ በኮቪድ 19 የተጠቁ ስድስት መንገደኞች መገኘታቸውን ተከትሎ ለአንድ ሳምንት በረራ እንዳያደርግ ታግዶ ነበር፡፡

በተቆጣጣሪው ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር ፖሊሲ መሰረት በኮቪድ የተጠቁ መንገደኞች ቁጥር አምስት ከደረሰ በረራው ለአንድ ሳምንት ይታገዳል ፡፡

የተጠቂዎች ቁጥር አስር ከደረሰ ደግሞ ለአራት ሳምንታት በረራ እንዲያቆም ይደረጋል ሲል ሻንጋይ ዴይሊ የአገሪቱን የአቪዬሽን ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል፡፡

በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጡ መንገደኞች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ህክምና እንዲያገኙ መደረጉም ተነግሯል፡፡

ካለፉት አራት ሳምንታት በኃላ በቫይረሱ የተያዙ ተጓዞች ቁጥር መጨመሩ ተነግሯል፡፡

ከሰኔ ጀምሮ እንደ ኤሮፍሎት ፣ ቻይና ኢስተርን ፣ ኢትሃድ ፣ ጁንያያ እና ስሪ ላንካ ያሉ አየር መንገዱች ጨምሮ ከአስር በላይ በረራዎች ተቋሙ እገዳ ጥሎባቸዋል፡፡

ከተማዋ ሰኞ ዕለት አምስት አዲስ ከውጭ የገቡ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን የመዘገበች ሲሆን ሁለት ህሙማን ካገገሙ በኋላ ከሆስፒታል እንደወጡ ማክሰኞ ጠዋት የሻንጋይ ጤና ኮሚሽን አስታውቋል ፡፡

እስካሁን ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡት 753 ተጠቂዎች መካከል 678 ሰዎች አገግመው ሲወጡ 75ቱ አሁንም ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው፡፡ ከውጭ የገቡ ስድስት የተጠረጠሩ ሰዎችም ምርመራ እያደረጉ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *