አሜሪካን ጨምሮ አራት ሀገራት በህንድ ዉቅያኖስ ላይ የጋራ የጦር ልምምድ ሊያደርጉ ነዉ፡፡

በሚቀጥለው ሳምንት አሜሪካ፣ ህንድ ፣ጃፓንና አወስትራሊያ በህንድ ውቂያኖስ ላይ የማላባር ልምምድ በሚል የጋራ የጦር ልምምድ ሊያደርጉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ልምምዱም የ4ቱን ሀገራት ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚረዳ የተገለፀ ሲሆን ቻይናን ለማስፈራራትም ይጠቅማል ነው የተባለው ፡፡

አውስትራሊያ በአራትዮሽ የደህንነት ውይይቱ ላይ የምትሳተፈው ከ2007 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነም ሲ ኤን ኤን በዘገባው ጠቁሟል፡፡

የአራትዮሽ ደህንነት ውይይቱ አሜሪካ ፣ ጃፓን ፣ አውስትራሊያ እና ህንድ መደበኛ ያልሆነ የስትራቴጂክ መድረካቸው ሲሆን በ4ቱ ሀገሮች መካከል የግማሽ መደበኛ ስብሰባዎችን እና መረጃዎችን ይለዋወጡበታል፡፡

የ4ቱ ሀገራት ጥምረት እንደ የሰሜን አትላንቲክ ስምምነት ድርጅት መደበኛ ወታደራዊ ጥምረት ባይሆንም ፣ አንዳንድ ሰዎች በእስያ-ፓስፊክ ውስጥ እየጨመረ ለሚሄደው የቻይና ተጽዕኖ እና የተቃጣ ጥቃት እንደ ሚዛን ማስጠበቂያ ሊወሰድ ይችላል ተብሏል፡፡

ማላባር በሕንድ እና በአሜሪካ መካከል የሁለትዮሽ እንቅስቃሴ ሆኖ ይጀመር እንጂ ጃፓንም እንደ ጎርጎሮሲያን ዘመን አቆጣጠር ከ2015 ዓመት አንስቶ ቋሚ አባል ሆና ቀጥላለች፡፡

በሁሉአገር አተሮ
ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *