የከተማ አስተዳድሩ ምክር ቤት 8ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ያካሄዳል፡፡
በ8ኛ አመት 1ኛው መደበኛ ጉባኤ የአስፈጻሚ አካላት የ2013 በጀት ዓመት የሶስት ወራት እቅድ አፈጻጸም እንደሚገመግም የምክር ቤቱ የፕሬስና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስዓለም እንቻለው ገልጸዋል፡፡
በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ በሚካሄደው መደበኛ ጉባኤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን እንደገና የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በማካሄድ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያስተላልፍ አቶ አዲስዓለም ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪ በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ልዩ ልዩ ሹመቶች እንደሚሰጡም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪ አስታውቋል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም











