ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ጥናት እና ምርምር ለማድረግ 100 ሚሊዮን ብር መመደቧን አስታወቀች።

ሀገሪቷ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን እና ባህርይውን ማየት የሚያስችል ሀገራዊ ጥናት ልታደርግ መሆኗን አስታውቃለች።

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የኮሮና ቫይረስ መረጃ ስትጠቀም የነበረው በአለም አቀፍ ደረጃ የሚወጡ ጥናቶችን እና መረጃዎችን ሲሆን ይህም ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘቡ አልነበሩም።

ስለሆነም የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤን ያገናዘበ ጥናት ነው የሚካሄደው።

ጥናቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን የመከላከል አቅማችን ምን ያክል እንደሆነ ለማወቅም የሚረዳ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህንን ለማድረግም ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ 45 ሳይንቲስቶች ይሳተፉበታል ተብሏል።
በተጨማሪም 7 የመንግስት እና የግል ተቋማት ጥናቱን ለማካሄድ ተመርጠዋል።

ከነዚህም መካከል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ መቀሌ ዩኒቨርስቲ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎችም ይገኙበታል።

ለመነሻ ያክል የጤና ሚኒስቴር 10 ማሊዮን ብር በጀት መድቧል። ሙሉ ጥናቱ ግን አንድ መቶ ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ ነው የተገለፀው።

እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ 7 ጥናቶችን አድርጋለች።
የአሁኑ ጥናት ግን እጅግ የተለየ እና በመላው ሀገሪቷ የሚደረግ ነው።

ጥናቱ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን ይህም እንደ ፈረንጆቹ በህዳር 2021 ዓ.ም የጥናቱ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.