የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሳህል ክልል ከፍተኛ ረሃብ እንደሚከስት አስጠነቀቀ፡፡

ለዓመታት በክልሉ ባለው ብጥብጥ እና አለመረጋጋት ሳቢያ በቡርኪናፋሶ ፣ በማሊ እና በኒጀር ወደ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ወደ ከፋ ረሃብ እያመሩ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

በማዕከላዊ ሳህል ክልል ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ወደ ለየለት የድህነት አዝቅት እንደሚያመሩም ተጠቁሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሳህል ክልል ባለው አለመረጋጋት በ2018 ወደ 70 ሺ ስዎች ከመኖሪያ መንደራቸው ተፈናቅለዋል።

ይህ አሃዝ በአሁኑ ስዓትም የተፈናቃዮች ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ወደ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን አድጓል፡፡

በማሊ ከ 288 ሺ በላይ ሰዎች፣ በኒጀር 265 ሺ በላይ ሰዎችና አንድ ሚሊዮን ያክል ሰዎች ደግሞ ከቡርኪናፋሶ ከከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

በአንድ ወቅት በሰሜን ማሊ አካባቢዎች ብቻ ተወስነው የቆዩት የአልቃይዳ እና የአይኤስ ታጣቂ ቡድኖች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሣህል አካባቢዎች ማለትም ወደ ቡርኪናፋሶ እና ኒጀር በመምጣት የተለያዩ ጥቃቶችና መፈናቀሎችን በመፈፀም ላይ ናቸው ፡፡

እነዚህ ፅንፈኛ ቡድኖች ከቀጠናው ነዋሪ ባሻገር በአካባቢው በተሰማሩ በፀጥታ ኃይሎችም ላይ ተደጋጋሚ ከባድ ጥቃቶችን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል ፡፡

በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የፀጥታ ሁኔታ እጅግ ሰብዓዊ ቀውስን እንደፈጠረ አልጀዚራ ዘግቧል።

የተባበሩት መንግስታት በሶስቱ ሀገሮች ውስጥ ያለውን የምግብ እጥረት ለመፍታት ለ13 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ለመስጠት ከሚያስፈልገው 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 34 በመቶውን ብቻ ነው እስካሁን መሰብሰብ የቻለው ፡፡

በየውለሰው ገዝሙ
ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.