የኢትዮጵያ ባንኮች አደጋ ቢደርስባቸው ተቀማጭ ገንዘባቸውን የሚመልስ የመድህን ፈንድ ማዘጋጀቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

እሳቸው በመግላቸው እንዳሉት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 105 ቢሊየን አዲስ ቁጠባ ተመዝግቧል ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 6 እጥፍ ነው ብለዋል።

ለዚህም ከባንክ የሚወጣን ጥሬ ገንዘብ መገደብ እንደ ምክንያት ያነሱት ከአዲሱ የገንዘብ ኖት ቅያሪ ጋር በተያያዘ ሲሆን እስካሁንም 37 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ ባለፉት ሶስት ወራት 33 ነጥብ 46 ቢሊየን ብር ከግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ መገኘቱንም ዶክተር ይናገር ተናግረዋል።

የሲሚንቶ እጥረት የተከሰተበት ምክንያት የውጭ ምንዛሬ እጥረት በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት 85 ሚሊየን ዶላር ለሲሚንቶ አምራች ድርጅቶች ድጋፍ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ሁሉም ባንኮች ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥም 55 ቢሊየን ብር ብድር መስጠታቸው የተገለጸ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 80 በመቶው ለግል ሴክተሩ የተሰጠ ነው።

የፋይናንስ ስርአቱ ጤናማ እንዲሆን ክትትል እየተደረገ መሆኑም በመግለጫው ተገልጿል።
ለዚህም የኢትዮጵያ ባንኮች አደጋ ቢደርስባቸው ተቀማጭ ገንዘባቸውን መመለስ የሚያስችል የመድህን ፈንድ መዘጋጀቱን ዶክተር ይናገር ተናግረዋል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.