ደቡብ ሱዳን በ2022 ሀገራዊ ምርጫ ለማከሄድ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች፡፡

የደቡብ ሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚነስትር የሆኑት ማርቲን ኢሊያ ሎሞሮ እንዳሉት፡ የሽግግር መንግስቱ መገባደጃ በሆነው የፈረንጆቹ 2022 ላይ ደቡብ ሱዳን ለጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ሱዳን የሰላም መረጋጋት እና አንድነትን ለማጠናከር ሲባል እ.ኤ.አ በ2018 ከተፋለሚ ሃይሎች ጋር ለ3 አመት የሚቆይ የብሔራዊ አንድነት የሽግግር መንግስት መመስረታቸው ይታወሳል፡፡

የዚህን የሽግግር መንግስት ስምምነት ማብቃትን ተከትሎ ነው ሎሞሮ፤ ሚራያ በተባል ሬዲዮ በ2022 ስምምነቱ እንዳበቃ ምርጫ እናካሂዳለን ሲሉ የተሰሙት፡፡

ነገር ግን አሁን በሃገሪቷ የሚሰተዋለው የላላ ስምምነት ደግሞ ምርጫውን በታሰበለት የጊዜ ገደብ ለመከወን እንቅፋት ሊሆን ይችላል ተብሎም ከወዲሁ እየተነገረ ይገኛል፡፡

ቢሆንም ሎሞሮ ምንም እንኳን በሀገራችን አልፎ አልፎ የሚታዩ አለመረጋጋቶች ቢኖሩም ምርጫውን ከማካሄድ ግን የሚያግደን አይኖርም ሲሉ ተናግረዋል ሲል ሱዳንስ ፖስት ዘግቧል፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
ጥቅም 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *