ሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአከፋፋዮች ችግር ምክንያት የሚጠበቅበትን ዳቦ ማምረት አለመቻሉን አስታወቀ።

በታሰበው ልክ ዳቦን በማምረት ወደ ተጠቃሚው ለማድረስ ያልቻልኩት በፋብሪካው ያልተጠናቀቁ የኮምሽን ስራዎች በመኖራቸው እንደሆነ ገልጿል።

በቀን ከ 1. 6 እስከ 1.7 ሚለየን ዳቦ ያመርታል ተብሎ ወደ ስራ የገባው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአሁኑ ሰዓት በቀን ወደ 1 ሚለየን ዳቦ በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

የፋብሪካው የኦፕሬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ኑረዱን ሙዘሚል ለኢትዮ ኤፍ ኤም ይሄን ብለዋል።

ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንዳይገባ ምርቱን ወደ ተጠቃሚዎች የሚያከፋፍሉ እና ሌሎች ተያያዥ የኮሚሸን ስራዎች ሙሉ በሙሉ አልተጠናቀቁም፡፡

ይሁን እንጂ ፋብሪካው ሲቋቋም ሊያመርት ከታቀደው አኳያ በአሁን ሰዓት እየተመረተ ያለው ዳቦ መጠነኛ የሚባል እንደሆነም አንስተውልናል፡፡

በፋብሪካው በቀን እየተመረተ ያለው 1 ሚለየን ዳቦ ለ 363 ማህበራት ተደራሽ እየተደረገ መሆኑንም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ይሁን እንጂ ወደ ማህበራቱ ተከፋፍሎ በከተማዋ በሚገኙ የሽገር ዳቦ መሸጫ ሱቆች ብቻ የሚቀርበው ይህ ዳቦ በጊዜ ማለቅና በበቂ ሁኔታ ለህብረተሰቡ ያለመድረስ ችግር መኖሩን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረን ባደረግነው ምልከታ ታዝበናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በየውልሰው ገዝሙ
ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *