በአዲስ አበባ መደበኛ ትምህርት ቢጀመርም በቴሌቪዥን እና ቴሌግራም ይሰጥ የነበረው ትምህርት ይቀጥላል ተባለ።

የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙለታ በከተማዋ ትምህርት መጀመር ጉዳይ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

ሀላፊው እንዳሉትም ትምህርት ቤቶች መደበኛ ትምህርት ቢጀምሩም የቴሌቪዥንና የቴሌግራም ትምህርቱ ድጋፍ ሰጪ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።

ትምህርቱን በሶስት ፈረቃ ለመስጠት ስራዎች የተጀመሩ ሲሆን ሰኞ፣ ረቡዕ፣ አርብ ፣ማክሰኞ ፣ሀሙስ እና ቅዳሜ ትምህርቱ ይሰጣል ተብሏል።

ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ እንዳይጋለጥ በክፍል 20 ተማሪ ብቻ እንዲማሩ ይደረጋልም ብለዋል።

ይሄንን ለማሳካትም 2 ሺህ 300 ተጨማሪ ክፍሎች ይገነባሉ ተብሏል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.