በአዲስ አበባ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ክሊኒክ ሊከፈት ነው።

በእያንዳንዱ ክሊኒኮች ውስጥም 4 ባለሙያዎች ይኖራሉ በ513 የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይከፈታል

የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙለታ በከተማዋ ትምህርት መጀመር ጉዳይ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

ሀላፊው እንዳሉትም ትምህርት ቤቶች መደበኛ ትምህርት ቢጀምሩም የቴሌቪዥንና የቴሌግራም ትምህርቱ ድጋፍ ሰጪ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።

ትምህርቱን በሶስት ፈረቃ ለመስጠት ስራዎች የተጀመሩ ሲሆን ሰኞ፣ ረቡዕ፣ አርብ ፣ማክሰኞ ፣ሀሙስ እና ቅዳሜ ትምህርቱ ይሰጣል ተብሏል።

ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ እንዳይጋለጥ በክፍል 20 ተማሪ ብቻ እንዲማሩ ይደረጋልም ብለዋል።

ይሄንን ለማሳካትም 2 ሺህ 300 ተጨማሪ ክፍሎች ይገነባሉ ተብሏል።

ተማሪዎችን አራርቆ ለማስተማር ሲታሰብ የመምህራን እጥረት ማጋጠሙን የተናገሩት ሀላፊው ተጨማሪ መምህራን እንደሚቀጠሩም አክለዋል።

ተማሪዎች ለንጽህና መጠበቂያ በቂ የውሀ አቅርቦት እንዲኖር 3 ሺህ ሮቶዎች እንዲገቡ ይደረጋልም ብለዋል

የመጽሀፍ ስርጭትን በተመለከተ ደግሞ 1 መጽሀፍ ለ1 ተማሪ በሚል መርህ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መዳረሱም ተገልጿል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *