የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እንዳስታወቀው በዘንድሮው ዓመት ከ400 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባው መርሀ ግብር ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።
ፈረቃ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች ግዴታ አይደለምም ተብሏል።
ርቀትን ጠብቆ በማስተማር ሁሉንም ተማሪ የማስተማር አቅም ያለው ትምህርት ቤት ያለ ፈረቃ ማስተማር ይችላል።
ይህ ሲሆን ግን በቢሮ ባለሙያዎች ተገምግሞ ካለፈ ብቻ እንደሆነ ቢሮው አስታውቋል።
በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም