የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ለካንሰር ህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች ማሰራጨቱን ገልጿል።
በኤጀንሲው የካንሰር ክምችት ባለሞያ አቶ አብዱራህማን አይረዲን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት 32 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ከ48 በላይ የሚሆኑ የካንሰር መድኃኒቶች ተሰራጭተዋል።
መድሃኒቶቹ ለቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፣ ለጥቁር አንበሳ፣ ለጦር ሃይሎች፣ ለህይወት ፋና፣ ለፈለገ ህይወት፣ ለደሴ ሪፈራል፣ ለጎንደር ዩንቨርስቲ፣ ለአዳማ ሜዲካል ኮሌጅ፣ ለጅማ ዩንቨርስቲ፣ ለሐይደር፣ ለነቀምት ሪፈራል፣ ለደብረብርሃን ሪፈራል እና ለአሰላ ሪፈራል ሆስፒታሎች መሰራጨታቸውንም አቶ አብዱራህማን ተናግረዋል።
በየውልሰው ገዝሙ
ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም











