ሐያት ሆቴሎች ኮርፖሬሽን በደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታወን ከተማ ስምንተኛ ቅርንጫፉን ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ።

ሐያት ሆቴሎች ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቅርንጫፉን ከሁለት ዓመት በፊት የከፈተ ሲሆን አሁን ደግሞ ስምንተኛ ቅርንጫፉን በደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታወን ከተማ ሊከፍት መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ገልጿል።

ሀያት ሪጀንሲ ኬፕታወን በሚል ስም የሚከፈተው ይህ ሆቴል የፊታችን ታህሳስ በይፋ ስራ እንደሚጀምር ተገልጿል።

ሆቴሉ 137 አልጋዎች ይኖሩታል የተባለ ሲሆን የሆቴሉ መከፈት በአፍሪካ በየዓመቱ በ6 በመቶ እያደገ ለሚገኘው የአፍሪካ ቱሪዝም አወንታዊ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

የCOVID-19 ወረርሽኝ የዓለምን የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ የጎዳ ሲሆን በተለይ የቱሪዝም ዘርፉ በእጅጉን የችግሩ ተጽእኖ እንዲያርፍበት ሆኗል፡፡

ሐያት ሬጀንሲ የኢትዮጵያን የሆቴል እና የቱሪዝም ገበያ ከ2010ዓ.ም ጀምሮ የተቀላቀለ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡

አህጉሪቱ በየጊዜው እየጨመረ ከሚሄደው የቱሪዝም እንቅስቃሴዋ ጋር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ያለ የንግድ ሁኔታን እየሳየች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ለሐያት ተመራጭ የኢንቨስትመንት ትኩረት እንደሆኑለትም በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.