ሳዑዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት መደበኛ ለማድግ በቅርቡ ትንቀሳቀሳለች የሚል ግምት እንዳለቸው የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን ገለፁ፡፡

የእስራኤሉ መከላከያ ሚንስትር ቤኒ ጋንትስ በትናንትናው እለት አሜሪካን ሲጎበኙ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት ሳውዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ በቅርቡ እንደምትንቀሳቀስ እምነት አለኝ በማለት ተናግረዋል፡፡

የእስራኤሉ ም/ል ጠቅላይ ሚንስትር እና መከላከያ ሚንስትር የሆኑት ጋንትስ ለኢብራይስጥ ሚዲያዎች የሰጡት ማብራሪያ አጭር ቢሆንም ‹በቅርቡ ሱዳን ቀጥሎ ደግሞ ሳውዲ አረቢያ ከሳጥናቸው ውስጥ ይወጣሉ› ሲሉ መደመጣቸውን ኤፒ ዘግቧል፡፡

ባለፈው ወር በዋሽንግተን የአይሁድ መንግስት እና የባህረ ሰላጤው አረብ መንግስታት ወደ መደበኛ ግንኙነቶች እንዲመለሱ ጥረት ቢደረግም የሳውዲ አረቢያ መሪዎች ፍላጎት ሳያሳዩ መቅረታቸው ይታወቃል፡፡

በወቅቱም የፊልስጤም መንግስት ከመፈጠሩ በፊት ከእስራኤል ጋር የነበረውን ግንኙነት መደበኛ እንደማያደርጉ በይፋ አረጋግጠውም ነበር፡፡

በደረሰ አማረ
ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.