አሜሪካ ለታይዋን አዲስ የጦር መሣሪያ መሸጧን ተከትሎ የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ቻይና አስጠነቀቀች፡፡

ታይዋን የመሣሪያ ሽያጩን ከአሜሪካ ብትቀበልም ከቤጂንግ ጋር ወደ የጦር መሳሪያ ውድድር የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ነው የገለፀችው፡፡

የትራምፕ አስተዳደር ለታይዋን የጦር መሳሪያዎችን በመሸጣቸው እና የዩኤስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በደሴቲቱ ጉብኝት በማድረጋቸው ቀድሞውኑ በደቡቡ ቻይና ባህር ፣ በሆንግ ኮንግ ፣ በሰብዓዊ መብቶች እና በንግድ ጉዳዮች ላይ አለመግባባቶች የነበረ ቢሆንም ይሄ ነገር መፈጠሩ በቤጂንግ እና በዋሽንግተን መካከል ያለውን ውጥረት አክሮታል፡፡

ቤጂንግ በመደበኛነት ይፋ ያልሆነ ቋት ሆኖ በሚያገለግለው የታይዋን ወሽመጥ መካከለኛ መስመር ላይ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ባለማብረር የቻይናን ሉዓላዊነት እንድትቀበል ታይዋን ላይ እየጨመረ የሚገኘውን ጫና ተግባራዊ አድርጋለች፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን አሜሪካ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ሽያጭ ለታይዋን ማፅደቋን ተከትሎ በሰጡት ምላሽ ሽያጩ በቻይና ውስጣዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት እንዳለው ገልፀው የቻይናን ሉዓላዊነት እና የፀጥታ ፍላጎቶችን በእጅጉ በመጉዳት ለታይዋን ኃይሎች ከባድ የተሳሳተ ምልክት ይልካል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧ፡፡

በመጨረሻም የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባዩ ድርጊቱን የቻይና-አሜሪካን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ ያበላሸ ነው ሲሉ ገልፀውታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሁሉአገር አተሮ
ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.