ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርጥ ዓለም ዓቀፋዊ ዩኒቨርሲቲ (Best Global Universities) ምድብ ውስጥ ተካተተ፡፡

ከ30 ዓመት በላይ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎችን ደረጃ በማውጣት የሚታወቀው “usnews & world report” በቅርቡ በ81 ሐገራት በጀመረው የትምህርት ተቋማት ጀረጃ አሰጣጥ መሠረት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከምርጥ 1 ሺህ 500ዎቹ ውስጥ ተካቷል፡፡

ደረጃውም ከዓለም 826ኛ፣ ከአፍሪካ 20ኛ፣ ከኢትዮጵያ 2ኛ ሆኗል፡፡

“usnews & world report” ደረጃውን ያወጣው 13 የተለያዩ መመዘኛ መስፈርቶች በመጠቀም መሆኑን በድረገጹ አስፍሯል፡፡

ዩኒቨርስቲው ባደረጋቸው ምርምሮች እና ከሌሎች ተቋማት ጋር እያደረገ ባለው የትብብር ስራ እንዚሁም ከሰራቸው የጥናት ስራዎች ምን ያህሉ ጥናቶች በሌሎች ዘንድ ተፈላጊ ናቸው በሚለውም መመዘኛ ነው ሊመረጥ የቻለው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *