ጌጅ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ በማስተርስ ድግሪ ያሰለጠናቸውን 511 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ላለፍት 16 ዓመታት የተማረ የሰው ሃይልን በማፍራት የድርሻውን በመዋጣት ላይ የሚገኘው ጌጅ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ በዛሬው እለት በሁለተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት 511 ተማሪዎች የመንግስት አካላት፣የተለያዩ እንግዶች፣የተመራቂ ቤተሰቦች እና የኮሌጅ የሴኔት አባላት በተገኙበት አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው መልእክትን ያስተላለፍት የኮሌጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሞገስ ግርማ የእለቱን ምሩቃን ለየት የሚያደርጋቸው በዓለማችንና በሃገራችን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረ ርሽኝ ተቋቁመውና አስቸጋሪውን የሕይወት ውጣ ውረድ አልፈው ለስኬትና ለውጤት በመብቃታቹ ነው ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

በዛሬው እለት ተቋሙ ካስመረቃቸው የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች ውስጥ 304 ወንዶች ሲሆኑ 207 ሴቶች ናቸው።

በየውልሰው ገዝሙ
ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.