በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኡራኤል አካባቢ ባለው የባቡር ሀዲድ ላይ ቀላል የእሳት አደጋ ተከሰተ።

ከላይ በተጠቀሰው አካባቢ በባቡር ሃዱ ላይ ጪስ ነገር መታየቱን ተከትሎ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው ደርሰው የማጥፋት ስራ ላይ ናቸው፡፡

በከተማዋ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በአካባቢ የተፈጠረው አደጋ ለማጣራትና በቁጥጥር ስር ለማዋል የእሳት አደጋ መኪናዎችና ሰራተኞች ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ተናግረዋል፡፡

አደጋው በስፍራው ከተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል።

በባቡር ሀዲዱ አካባቢ የተፈጠረው ጢስ መነሻው ምን እንደሆነ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን በስፍራው ከሚገኙ የእሳት አደጋ ሰራተኞች መረጃው ወደ ማዕከል እንደተላከ ለህዝብ ይፋ እናደርጋለንም ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ግን የእሳት አደጋ መኪኖች ወደ ስፍራው ያቀኑ ሲሆን የተፈጠረውም አደጋም ቀላል የሚባል እንደሆነ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአካባቢው ስለተፈጠረው ጭስ ወደ ፊት የተጣሩ መረጃዎች እንደደረሱን የምናቀርብ ይሆናል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *