ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሴቶች አመራር ማዕከል ልታቋቁም መሆኑን አስታወቀች፡፡

በኢትዮጵያ የአፍሪካ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የአመራር ማእከል ሊቋቋም ነው ተብሏል፡፡

የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በ10 ዓመቱ መሪ ዕቅድ ዙሪያ ከሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት የአፍሪካ ሴቶች አመራር ማእከል ሊቋቋም መሆኑን አስታውቋል፡፡

ማእከሉ የአፍሪካ ሴቶች ስልጠና የሚወስዱበት ጥናትና ምርምር እንዲሁም የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ይሆናል ነው የተባለው፡፡

በሚቋቋመው የአመራር ማእከል በአፍሪካ ታዋቂ እና ስመጥር የሆኑ ሴቶች ልምዳቸውን ለሌሎች ሴቶች እንዲያካፍሉ እድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ሴቶች የሚደርስባቸውን ተጽእኖ ለመፍታትም ይህ ማእከል ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው የተባለው፡፡

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የሴቶች የአመራር ማእከል በማድረግ ከሀገር አልፎ ለአህጉር ብሎም ለአለም ተምሳሌት የሆኑ የሴት አመራሮችን ለመፍጠር የአፍሪካ ሴት አመራሮች ማእከል በማቋቋም ብቁ የሆኑ 10 ሺህ ሴቶችን ለማፍራት መታቀዱን ነው የተገለጸው፡፡

ሴቶች በህግ አውጪነት በህግ አስፈጻሚነት እንደዚሁም በህግ ተርጓሚነት የሚኖራቸውን ሚና ለማረጋገጥ በ2022 ድርሻቸው 50 ከመቶ ለማድረስ እንደሚሰራ ተገልጻል፡፡

ማእከሉ ለማቋቋምም እስከ 500 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚያስፈልግም የተገለጸ ሲሆን ወጪውን የኢትዮጵያ መንግስት ከሌሎች ለጋሽ ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት የታሰበ ሲሆን የማዕከሉ ዲዛይን በመጠናቀቅ ላይ ነው ተብሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.