የአረብ ሃገራት በፈረንሳይ ምርቶች ላይ ያለመጠቀም አድማ እያደረጉ ነዉ፡፡

የፈረንሳይ ምርቶችን ያለመጠቀም አድማ የተቀሰቀሰዉ የፈረንሳዪ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስተያየትን ተከትሎ ነዉ፡፡

በፈረንሳይ ሳሙኤሊ ፓቲ የተባለ የታሪክ መምህር ሲገደል ገዳይ ተብሎ የተጠረጠረዉ ግለሰብ የነብዩ መሃመድ ምናባዊ የካርቶን ምስል አሳይቶ ነበር፡፡

ይህን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ማክሮን መምህራችንን ያሳጡን አክራሪ እስላማዊ ታጣቂዎች ናቸዉ፤እነርሱ የወደፊት መልካም ህልማችንን ሊነጥቁን ይፈልጋሉ፤እኛ ግን ይህ እንዲሆን አንፈቅድላቸዉም ብለዉ ነበር፡፡

ይህን ንግግራቸዉን ተከትሎ በተለያዩ ሀገራት ዜጎች ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን የፈረንሳይ ምርቶችን አለመጠቀም ደግሞ እየተወሰደ ያለ እርምጃ ነዉ፡፡

በኩዌት፣ዮርዳኖስና ኳታር ዜጎች በቀዳሚነት እርምጃዉን የወሰዱ ሲሆን እነርሱን ተከትለዉ ደግሞ ሊቢያ፣ሶሪያና የጋዛ ሰርጥ አጋባቢዎች እርምጃዉን ተቀላቅለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ማክሮን የአረብ ሀገራት ዜጎች ከዚህ ድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ ገልጸዉ፣ ፈረንሳይ የሁሉሉንም እምነት በሚገባ ታከብራለች፤ከሁሉም ግን የሰዎች ደህንነት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባዋል ብለዋል፡፡

የቱርክና የፓኪስታን ፖለቲከኞችም ቢሆኑ የፕሬዝዳንት ማክሮንን ንግግር ተችተዋል፡፡

ንግግራቸዉ ጅምላ ፈራጅና የእምነት ነጻነትን የሚጋፋ ነዉ ማለታቸውን ዘ-ጋርዲያን ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *